የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የተገነቡ ፓርኮች መልካም የልማት ምሳሌ መሆናቸውን በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርግ የነበረው የጅቡቲ ልዑክ ገለጸ

By Meseret Awoke

February 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ ፓርኮች ለጎረቤት ሀገራት ጭምር መልካም የልማት ምሳሌ መሆናቸውን በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርግ የነበረው የጅቡቲ ልዑክ ገለጸ።

ልዑኩ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው የኢትዮ ጅቡቲ ፎረም ላይ ሲካፈል የቆየ ሲሆን ዛሬ እንጦጦ ፓርክን እና አንድነት ፓርክን ጎብኝቷል።

ከጅቡቲ ቱሪዝም፥ የንግድ ምክርቤት፥ ቱር እና ትረቭል ኦፕሬተሮች እንዲሁም የሆቴል ባለቤቶች የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች የኢትዮጵያ መንግስት የገነባቸውን ፕሮጀክቶች አድንቀዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነትና አመራር ሰጪነት የተሰራው ስራ ለጎረቤት ሀገራትም የሚተርፍ ነው ብሏል ልዑኩ።

የከተማ ፓርኮች እና የአረንጓዴ ፕሮጀክቶች መልካም ልምድ የወሰድንባቸው ናቸውም ነው ያለው ልዑኩ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!