የሀገር ውስጥ ዜና

መሠረተ ልማትን በማሟላት ከተሞችን ዘመናዊ ለማድረግ ይሰራል – አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

By Meseret Awoke

February 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ርዕሰመስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር የተመራው የፌደራል እና የክልሉ አመራሮች በጎዴይ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙትን የልማት ፕሮጀክቶች ጎበኙ።

ከ475 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ ያለን የጎዴይ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

ፕሮጀክቱ በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን የግንባታ ተቋራጭ የሚገነባ ሲሆን የዚህ ፕሮጀክት ወጪ በሶማሌ ክልል የሚሸፈን ነው።

የጎዴይ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ለ107 ሺህ ህዝብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል ተብሏል።

አሁን ላይ የሲቪል ስራው 45% መድረሱንና 45 ኪ.ሜ ከዋቢ ሸበሌ ወንዝ ወደ ከተማ የሚዘረጋው ማከፋፈያ 23 ኪ.ሜ እንደተገነባ በገለፃው ወቅት የፕሮጀክቱ ሥራ ተቋራጮች ተናግሯል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት የነበሩትን ችግሮች በመቅረፍ በስምምነቱ መሠረት አጠቃላይ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅና አሳስበዋል።

ርዕሰመስተዳድሩ በ298 ሚልዮን ብር ወጪ በጎደይ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ሶስት የአስፓልት መንገድ ስራዎችን የተጎበኙ ሲሆን፣ መንገዶቹ ከተማውን ግንባታው ከተጀመረው የጎደይ ኤርፖርት እንደሚያገናኙና የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት እንደሚያዘምኑ ተገልጿል።

የመንገድ ሥራውን አመል የግንባታ ሥራ ተቋራጭ የወሰደ ሲሆን በአጠቃላይ ግንቦት 2013 ዓ.ም ላይ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በተመለከቱት የመንገዱ የግንባታ ሥራ መደሰታቸውን ገልፀው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!