የሀገር ውስጥ ዜና

በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

By Meseret Awoke

February 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አመራርና ሰራተኞች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አካሄዱ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጤናማና የተማረ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያግዛል ያሉት የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ዑባህ አደም የአካል ብቃት እንቅስቃሴው በቀጣይነት ዩኒቨርስቲው ባሰለጠናቸው ሙያተኞች ወር በገባ በመጀመሪያዉ ሣምንት በተከታታይነት እንደሚደረግ አስታውቀዋል ።

የዩኒቨርስቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን በበኩላቸው ስፖርታዊ እንቅስቃሴው ጤናን ከመጠበቅ አኳያ ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የሚኖረው ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን ሲያከናውኑ ያገኘናቸው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰቦች በበኩላቸው ይህን መሰል መድረክ መዘጋጀቱ ጤናቸውን ለመጠበቅ እንደሚያስችላቸው ገልፀዋል። በዩኒቨርስቲው ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ሁሉም የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላትና የሀገር አቀፍ በጎ ፈቃደኛ አሰልጣኞችን ባሳተፈ መልኩ መካሄዱ ለየት ያደርገዋልም ተብሏል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!