የሀገር ውስጥ ዜና

ሶስት የልማት ድርጅቶች ባለፉት ስድስት ወራት ከ200 ሚሊየን በላይ አተረፉ

By Tibebu Kebede

February 15, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማምረቻና ኢነርጂ ዘርፍ የተሰማሩ ሶስት የልማት ድርጅቶች በመጀመሪያው አጋማሽ ዓመት ከ200 ሚሊየን ብር በላይ አተረፉ።

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ካሉት የልማት ድርጅቶች መካከል ሶስት የልማት ድርጅቶች ባለፉት ስድስት ወራት ከታክስ በፊት 117 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ትርፍ ለማግኘት አቅደው 200 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ማትረፍ መቻላቸው ተጠቁሟል።

የልማት ድርጅቶች ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ እና የኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር ሲሆኑ ÷ ድርጅቶቹ 665 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ሽያጭ በማከናወን በመቻላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

ከሦስቱ ድርጅቶች መካከል ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ የውጭ ሽያጭ የሚያከናውን ሲሆን÷ 200 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት አቅዶ 342 ሺህ 556 የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ችሏል፡፡

በግምገማው የድርጅቶቹ የኦፕሬሽን ፣ የፋይናንስ ፣ የፕሮጀክት ዕቅድ አፈጻጸሞች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችም አጽንኦት ተሰጥቷቸው መታየታቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ለተገኘው ጥሩ አፈጻጸም  ምሥጋና አቅርበው ይህ ጥረት በቀጣዩ የበጀት ዓመቱ ወራትም ተጠናክሮ በመቀጠል የዓመቱን የድርጅቶቹን ግቦች በተሻለ አፈጻጸም እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!