አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ዜልቶቭ እና ከስዊዘርላንድ አምባሳደር ክርስቲያን ዊንተር ጋር ተወያዩ፡፡
አምባሳደሩ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይቱም አምባሳደር ይበልጣል በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ መንግስት ያለውን አቋም አስረድተዋል፡፡
የሩሲያው አምባሳደር በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው፥ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለባቸውና የሃገራት ሉዓላዊነት መከበር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ ጉዳዮች ፖለቲካዊ መደረግ የለባቸውም የሚል የፀና አቋም እንዳላትም ገልጸዋል፡፡
የስዊዘርላንድ አምባሳደርም በተመሳሳይ በአምባሳደሩ ስለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው፥ በገለፃው ስለተጠቀሱት ጉዳዮች ሰፊ ግንዛቤ እንዳገኙ መናገራቸውን በሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!