አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አለም አቀፉዊ ሴቶችን በሳይንስ ቀን በኢትዮጲያ ተከብሯል፡፡
“ሴት ሳይንቲስቶች ኮቪድ-19ን ለመዋጋት ግንባር ቀደም ናቸው” በሚል አለም አቀፋዊ መሪ ቃል መሰረት የኢትዮጲያ ስፔንስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን በኢንስቲትዩት ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በአለም ለ6ኛ ጊዜ የሴቶች የሳይንስ ቀንን አክብሯል፡፡
በክብረ በዓሉ ለእቴጌ መነን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴት ተማሪዎች ሳይንሳዊ ግንዛቤ የመፍጠሪያ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን፤ ታላላቅ ሴት ሳይንቲስቶች ለሴት ተማሪዎቹ ልምዳቸዉን አካፍለዋል፡፡
ሳይንሳዊ የተግባር ልምምድ ፤ ዉይይት እንዲሁም የኮከብ ምልከታ ፕሮግራምም በእለቱ እንደተካሄደ ወይዘሮ ፍሬህይወት ጋሮምሳ ከኢንሰቲትዩቱ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ጊዜያዊ ዳይሬክተር መግለጻቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!