የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሐረር ከተማ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Meseret Awoke

February 16, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በሐረር ከተማ እየተገነቡ ያሉ እና ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

የስራ ኃላፊዎቹ በከተማዋ የስራ ዕድል ፈጠራ የስልጠና ማዕከል፣ የአርሶ አደር የገበያ ማዕከል፣ አስፓት መንገድ ግንባታ፣ የዕደጥበብ ማዕከል፣ የአብደላ ሸሪፍ የግል ሙዚየም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በሀረር ከተማ በ300 ሚሊየን ብር እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሀረሪ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልሀኪም አብዱልማሊክ በጉብኝቱ ወቅት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሴክተር መስሪያ ቤቶች ውይይት መድረክ ነገ በሐረር ከተማ ይካሄዳል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም https://t.me/fanatelevision ትዊተር https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!