አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የአድዋ ድል በዓል በጋምቤላ ከተማ በስፖርታዊ ውድድር ተጀምሯል፡፡
“አድዋ የህብረ-ብሔራዊ አንድነት አርማ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
ነገ በይፋ የሚጀመረው ክብረበዓሉ በጋምቤላ ክልል ሲካሄድ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡
በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሙድ ኡጁሉ እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡
በነገው ዕለትም የፓናል ውይይቶች እና ስፖርታዊ ትዕይንቶች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል፡፡
በጸጋዬ ንጉስ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!