አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የጤና ድርጅት በኢትዮጵያና የካናዳ መንግስት ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለሟሟላት የሚያስችል ድጋፍ ይፋ አደረጉ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ አቅምን ለማጠናከር ያለመው ይህ ድጋፍ 9 ነጥብ 9 ሚሊየን የካናዳ ዶላር ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለሴቶች፣ ህጻናት እና ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችልም ታምኖበታል፡፡
እንዲሁም መሰረታዊ የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ በመተግበር የህብረተሰቡን ተጋላጭነትን ለመቀነስ እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቦሬይማ ሃማ ሳምቦ የካናዳ መንግስትን አመስግነዋል፡፡
ተወካዩ ድጋፉ መሰረታዊ የጤና አቅርቦትን ከማሻሻል በተጨማሪ የጤና ስርዓቱን ያዘምናል ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!