የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  የቦርድ አመራሮች  ጋር ተወያዩ

By Meseret Demissu

February 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  የቦርድ አመራሮች  ጋር ተወያዩ።

በከተማዋ የታየው  ሰላማዊ እንቅስቃሴው ዘላቂ እንዲሆን   እና ግብረገብነት እንዲጎለብት የሁሉም ሃይማኖት ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ሚና  እንዲወጡ ወይዘሮ አዳነች በውይይቱ ገልጸዋል፡፡

የሃይማኖት ተቋማቱ ሰላም እንዲሰፍን እና ህብረተሰቡ ባለው አቅም እንዲረዳዳ እና እንዲተጋገዝ ከመንግስት ጎን በመቆም ያደረጉት  አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ÷  ምእመናኑን ስለሰላም ፣ስለአንድነት እና መቻቻል እያደረጉትን ያለውን እንቅስቃሴ  በይበልጥ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡

በሃይማኖት ተቋማት በኩል የሚታየውን ህገወጥ የመሬት ወረራ ዝንባሌን በማስቆም እራሳቸው  የሃይማኖት ተቋማቱ ለህብረተሰቡ ምሳሌ ሆነው የወረሩትን በራሳቸው ወደ መሬት ባንክ እንዲመልሱ ምክትል ከንቲባዋ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጲያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ  የቦርድ አመራሮች በበኩላቸው ÷የከተማ አስተዳደሩ ሁሉንም ሃይማኖት ተቋማት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ በመመለስ፣ ህግ እና ስርዓት እንዲከበር ፣ የህብረሰቡን አንገብጋቢ ጥያቄዎች እንዲመለሱ  እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው የከተማ አስተዳደሩ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እንዲሁም ለድሆች ትኩረት በመስጠቱ ማመስገናቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!