አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጀሪያ የቬትናም አምባሳደር አንጉየን ታን ቪን እንዲሁም በአልጄሪያ የኮንጎ ሪፐብሊክ አምባሳደርና የአፍሪካ አምባሳደሮች ዲን ጃን ፔ ሉዌቦ ጋር በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይቱ መንግስት በትግራይ ክልል ያከናወነውን የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁንና በክልሉ የሰብዓዊ ዕርዳታ በመንግስትና በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ትብብር እየተሰራጨ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር የተያያዙ ክሶችን መንግስት በልዩ ትኩረት የሚከታተለውና በወንጀል የተሳተፉ አካላትን ለህግ እንደሚያቀርብም ጠቁመዋል።
በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ አካላት ባለሥልጣናት በስፍራው ተገኝተው ጉብኝት ማድረጋቸውንና በቀጣይ ሥራዎችም ዙሪያ ከመንግሥት ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የተከሰተው የድንበር ግጭትም ታሪካዊ ዳራውን በመግለጽ ኢትዮጵያ ሱዳን ወደ ቀድሞዋ ሥፍራ ተመልሳ ድርድሩ መካሄድ እንዳለበትና ችግሩ ሊፈታ የሚችለውም በውይይት ብቻ መሆኑን እንደምታምን ገልጸዋል፡፡
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያላትን የፍትሃዊ ተጠቃሚነት አቋም ለአምባሳደሮቹ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!