የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ የፓርቲውን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት አስታወቀ

By Abrham Fekede

February 18, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ብልጽግና ፓርቲ የፓርቲውን ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት በይፋ አስተዋወቀ፡፡

ምልክቱን በይፋ ያስታዋወቁት የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ኡሙድ ኡጁሉ ናቸው፡፡

ፓርቲው ማኒፌስቶውንና የምርጫ መወዳደሪያውን ባስተዋወቀበት ወቅት ስለማኒፌስቶው ዓላማ ግልጽ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ የፓርቲውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የካቲት 8 ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በአዲስ አበባ በተካሄደው የዕውቅና ስነስርዓት ላይ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ነበር የተካሄደው፡፡

በፀጋዬ ንጉስ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!