a Series of electrical transmission tower with power lines criss crossing at sunset.

የሀገር ውስጥ ዜና

ኬንያን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ በሰኔ ወር እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ

By Abrham Fekede

February 18, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ በሰኔ ወር እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ፡፡

ይህንን ያስታወቁት የሀገሪቱ ኢነርጂ ሚኒስትር ቻርለስ ኬተር ናቸው፡፡

የኢነርጂ ሚኒስትሩ በመጪዎቹ ሦስት ወራት ከማዕከላዊ ቋት ጋር ለማገናኘት ዝግጅት መጠናቀቁን ነው ይፋ ያደረጉት፡፡

የተዘረጋው መስመር ከምስራቅ አፍሪካና ከመካከለኛ አፍሪካ ከሚገኙት መስመሮች መካከል ትልቁ መሆኑን ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማትና የኬንያ መንግስት ለመስመር ዝርጋታው 620 ሚሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያገናኘው መስመር ከዚህ ቀደም መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!