የሀገር ውስጥ ዜና

“የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል የንቅናቄ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ

By Tibebu Kebede

February 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል የንቅናቄ ኮንፈረንስ በድሬዳዋና በደቡብ ክልል የተለያዩ ዞኖች መካሄድ ጀምሯል፡፡

መድረኩ የሴቶችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ ውስጥ እንቅፋት የሚሆኑ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣትና በግልጽ በመነጋገር በየደረጃው ችግሮች እየተፈቱ እንዲሄዱ የሚረዳ እንዲሁም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና ፖለቲካዊ ተሳትፎ በመሰረታዊነት ለመመለስ የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

መድረኩ በቀጣዮቹ ቀናትም በመላው ሀገሪቱ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!