አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉባኤው በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ጋባዥነት የኢፌዴሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ኂሩት ካሳው ንግግር አድርገዋል።
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባው አያሌው ስለ አድዋ ታሪክ የውይይት መነሻ ሀሳብ አቅርበዋል።
በጉባኤው በክራር የታጀበ ግጥም፣ ሽለላ እና ፉከራ ከሀገር ፍቅር ቀርቧል።
ሌሎች ጥናታዊ ጽሁፎችም ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ ዲፕሎማቶች፣ የታሪክ ምሁራንና የዲያስፖራ አባላት መታደማቸውን ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!