የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል ለሲዳማ ክልል 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Meseret Demissu

February 22, 2021

አቶ ሽመልስ ይህን የገለጹት በሲዳማ ክልል የመንግሥት ይፋዊ ምሥረታ ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።

በዚህ ንግግራቸው ለሲዳማ ክልል የምስረታ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ ብለዋል።

የሲዳማ ህዝብ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ቋንቋና ባህል የሚጋራ ህዝብ ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ ።

የኢትዮጵያዊነት መንገድ እኩልነት፣ ወንድማማችነት፣ ነፃነት፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ነው፤ ከዚህ ውጪ ያለው መንገድ ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ዳግም ወደ ጥፋት መንገድ አትሄድም፣ኢትዮጵያ አፍራሾቿን ሁሉ እያፈረሰች አንድነቷን ጠብቃ ትኖራለችም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።

ኢትዮጵያዊነት የሁሉንም ቋንቋ በማክበር በእኩልነት ጠብቆና አንዱ አንዱን እየጠበቀ በጋራ በመኖር ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊነቷን እያረጋገጠች፣ አንድነቷን እያጠናከረች ብልጽግናዋን ታረጋግጣለች ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ለማድረግም በጋራ እንሰራለንም ነው ያሉት።

የሲዳማ ክልል የፍቅር ውብ ባህል ያለው ከሁሉም ጋር  በፍቅር የሚኖር ህዝብ ነውም ብለዋል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የእለቱ የክብር እንግዳ  አቶ አደም ፋራህም የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ የኢፌዴሪ ህገ መንግስትን መሰረት በማድረግ  ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲመሩና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያ ተጠቃሚነታቸውን እንዲያረጋግጡ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

የክልል መንግስታት የህዝቦችን የእርስ በእርስ ወንድማማችነትና አንድነት  የሚያጠናክሩ ስራዎችን አጠናክረው መቀጠል አለባቸውም ብለዋል በንግግራቸው።

በዚህም የሲዳማ ክልል ለማቋቋምና በትግራይ  ክልል ጁንታው የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለመገንባት ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር  ጎን በመቆም ላሳዩት ድጋፍም አመስግነዋል፡፡

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ምላሽ አግኝቶ ለዚህ ቀን በመብቃታችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ከጥንት ጀምሮ የሲዳማ ህዝብ ሲጠይቅ የነበረውን ጥያቄ በሀገሪቱ የመጣው ለውጥና የለውጡ አመራሮች መልስ ሰጥተውታል ለዚህም ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋልም ነው ያሉት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!