አዲስ አበባ ፣ የካቲት 15 ፣ 2013 (ኤ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፣ በቤኒሻንጉል፣ በሃረሪ፣ በጋምቤላ እና ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች የእጩዎች ምዝገባ የሚጠናቀቀው የካቲት 21 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን ገለጸ።
ይህንንም አውቃችሁ የጊዜ ገደቡ ከማለፉ በፊት የእጩዎች ምዝገባ እንድታጠናቀቁ ጥሪያችንን እናቀርባለን ሲል ቦርዱ አስታውቋል።
ቦርዱ አያይዞም በአዲስ አበባ አስተዳደር የሚገኙ የምርጫ ክልል ቢሮዎችን ዝርዝር የመገኛ አድራሻ ለማግኘት የሚፈልጉ ሁሉም የፓለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርዱ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ከዜናው ስር በሚገኘው ማስፈንጠሪያ በመጫን ዝርዝር አድራሻውን ማየት እንደሚችሉ ገልጿል።
በተጨማሪ ም አስፈጻሚዎችን ለማነጋገር የሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካሉ ደግሞ አድራሻቸውን ከቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስራ ክፍል መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ቦርዱ በፌስ ቡክ ገጹ ላይ አስቀምጧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!