የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል – ንግድ ቢሮ

By Abrham Fekede

February 22, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እና መሰል ህግ ወጥ በሆነ የንግድ ተግባራት ላይ በሚሳተፉ ነጋዴዎች ላይ የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ ይህንን ያሉት እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት በተገመገመበት ወቅት ነው፡፡

አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣምና ዋጋን ለማረጋጋት የሚያስችሉ ተግባራት እየተሰራ መሆኑንም የቢሮው ሃላፊው አብራርተዋል፡፡

በተለይ መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንና አንስተዋል፡፡

በዚህም ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሊትር ፓልም ዘይትና ፈሳሽ ዘይት እንዲሁም 106 ኩንታል ስኳር በህገወጥ መልኩ ተከማችቶ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንዲሰራጭ እተደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

እስካሁን በተደረገው ቁጥጥርና ክትትል ከ60 ሺህ በላይ የንግድ ተቀማት ላይ የበር ለበር ክትትልና ቁጥጥር መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በ2 ሺህ 859 የንግድ ተቀማት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው መግለጻቸውን ከንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!