አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከ50 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ሕፃናት አፍ በፈቱበት ቋንቋ እየተማሩ ይገኛሉ ተባለ፡፡
በሰመራ ሲካሄድ በቆየው 11ኛው “በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን” የማጠናቀቂያ መርሐ ግብር ተካሄዷል፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመናገር ቀን በዓል በአፋር ሰመራ ሲከበር በክልሉ የባህል ቡድን በተለያዩ የመድረክ ዝግጅቶች ስነስርዓቱን ማድመቁ ተገልጿል፡፡
በበዓሉ መክፈቻ ላይ የክልሉ አፌ-ጉባኤ ወይዘሮ አሚናት ሴኮ እና የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ መሃመድ ጉርባኢስ ተገኝተዋል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ ከስምንት ያላነሱ ጥናታዊ ጽሑፎች ከዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ ምሁራን ቀርበው ገለፃና ውይይቶች ተደርጎባቸዋል፡፡
በዋናነት በቋንቋ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ በአዲሱ የስርዓተ-ትምህርት ስርዓት አማካይነት በየአካባቢው የሚካሄዱ የመማር ማስተማር ሂደቶች ቋንቋዎቻችንን የማበልጸግ፣ የማልማትና የመጠበቅ ሥራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ የሚመለከታቸው አካላት ኃላፊነታቸውን ወስደው ያለ ምንም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሙያዊ ሥራዎች እንዲሰሩ ውይይቶች መካሄዳቸው ነው የተጠቀሰው፡፡
በሙያዊ ስነምግባር እንዲያከናወኑ ማበረታታት እንደሚገባ በማሳሰብና ነፃ ሀሳቦች የተንፀባረቁበት ሆኖ ነው የተቋጨው፡፡
በመጨረሻም የበዓሉ ተሳታፊዎች የአፋር ባህል ማዕከል ሙዚየምን በመጎብኘት መርሐግብሩ መጠናቀቁን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን