አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የማዕድን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ የተመራ የልዑካን ቡድን በምዕራብ አፍሪካዊት ሀገር ማሊ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡
ቡድኑ በማሊ ካይስ ሪጅን ሳዲዮላ በተባለ ቦታ ያለውን የወርቅ ማምረቻ ቦታ ለመጎብኘትና በዋናነት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ስለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት፣ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ እና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በተያያዘ በኩባንያውና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ልምድና ተሞክሮ በመቀመር ተግባራዊ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
የመስክ ጉብኝት በማዕድን ማውጫ፣ የወርቅ ማምረቻ ፋብሪካ፣ የጥናት ቦታ፣ እንዲሁም ኩባንያው ባስገነባው የጤና ተቋም ጉብኝት ተካሂዷል፡፡
የማዕድን ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ወይዘሮ ስመኝ ውቤ በጉብኝቱ ወቅት ለተገኙ የውጭ ሚዲያዎች ስለጉብኝቱ ዓላማ፣ ስለ ኢትዮጵያ የማዕድንና ነዳጅ ሀብት እንዲሁም ልዑካኑ ከጉብኝቱ የቀሰመው ተሞክሮ እና ወደፊት ከኩባንያው ጋር በጋራ ሊተገበሩ የሚገባቸውን ነጥቦች አስረድተዋል፡፡
ልዑኩ በተለይም ከክልሉ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርከኖች የተውጣጡ አመራሮች በዘመናዊ መንገድ የወርቅ አመራረት፣ የማህበረሰብ ተጠቃሚነት እና የአካባቢ ጥበቃን በተመለከተ ልምድና ተሞክሮ ማግኘታቸው ተሰምቷል፡፡
አሊይድ የወርቅ ኩባንያ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ፣ አሶሳ ዞን፣ ኩርሙክ ወረዳ ዲሽ እና አሻሽሬ በተባሉ ቦታዎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሊለሙ የሚችሉ ሁለት የወርቅ ክምችት ምርመራ በማድረግ በቅርቡ ወደ ልማት ለመሸጋገር የምርት ፈቃድ ለመውሰድ የተዘጋጀ ኩባንያ መሆኑን ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ