የሀገር ውስጥ ዜና

ለ135 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ትግራይ ክልል ገብተው የሰብአዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲዘግቡና እንዲያግዙ ፈቃድ ተሰጠ

By Tibebu Kebede

February 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ላመለከቱ እና ዓለም አቀፍ መመዘኛውን ላሟሉ የ11 ዓለም አቀፍ የሚዲያ አባላትን ጨምሮ ለ135 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ሰራተኞች ወደ ትግራይ ክልል በመግባት የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ እና እንዲዘግቡ ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

መንግስት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውና ቀደም ሲል በሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው ድጋፍ ይደረግላቸው የነበሩ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎችን ጨምሮ የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎች ልየታ ተደርጎ እንደነበር የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጅ በማንኛውም ሁኔታ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል የተባሉ ወገኖችን በማካተት ለ3 ነጥብ 1 ሚሊየን ወገኖች ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም ነው ያስታወቀው፡፡

ሚኒስቴሩ ለወገኖች ለመድረስ በተደረገው ርብርብ ለማገዝ ለተሳተፉ አካላትም ምስጋናውን አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!