የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

February 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከእንግሊዝ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጀምስ ዱድሪጅ ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸው ወቅትም በጋራ ጉዳዮች እንዲሁም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ላይም መክረዋል።

በተጨማሪም በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በሚገኝበት ደረጃ ላይም ምክክር አድርገዋል።

አምባሳደር ተፈሪ በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍና ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ባላቸው ተደራሽነት ዙሪያም ለሚኒስትሩ ገለጻ አድርገዋል።

እንዲሁም ከትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እየተሰራጨ ያለውን ሃሰተኛ መረጃ መከላከል ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተም ገልጸውላቸዋል።

በውይይቱ ወቅት አምባሳደር ተፈሪ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከት ማጣራት እንደሚደረግና በጉዳዩ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑም አረጋግጠውላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!