የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል የስራ ኃላፊዎች በአዳማ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Meseret Awoke

February 26, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል የስራ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራ ልዑክ በአዳማ ከተማ ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱም የኦሮሚያ ክልል የሴክተር መስሪያ ቤቶች የስራ ኃላፊዎች እና የተለያዩ ከተሞች ከንቲባዎች ተሳትፈዋል፡፡

ልዑኩ የአዳማ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ህንፃን በመመረቅ በቴክኖሎጂ የታገዙ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!