አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለሁለንተናዊ ብልጽግና በሚል ሃሳብ የሴቶች የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ።
በመድረኩ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ሴቶች በማኀበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መጠናከር አለባቸው ብለዋል።
በሀገሪቱ ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መመሪያዎች፣ ሕጎችና ደምቦች በአግባቡ ተሰንደው መቀመጣቸውንም አንስተዋል፡፡
እነዚህን በአግባቡ በመጠቀም ሴቶች ለሀገራዊ ብልጽግና ተግተው ሊሠሩ ይገባልም ነው ያሉት በንግግራቸው፡፡
በመድረኩ ላይ 125ኛውን የአድዋ ድል በዓል የሚዘከር ሥነ ሥርዓትም መካሄዱን አብመድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!