የሀገር ውስጥ ዜና

345 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ተመለሱ

By Tibebu Kebede

March 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)345 ዜጎች ከሳዑዲ ዓረቢያ ጂዳ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ፡፡

ከተመላሾቹ መካከል 300 ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ህጻናት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ዜጎቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!