አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች አራተኛው ተከታታይ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ የምርጫ ምልክት የወሰዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮችና የምርጫ ቦርድ አመራሮች ተገኝተዋል።
ውይይቱ በዋናነት የዕጩዎቸ ምዝገባ ሂደት ያለበትን ሁኔታ፣ የቀረቡ አቤቱታዎችና የተሰጡ የመፍትሄ ምላሾችን የሚዳስስ እንደሆነ ተገልጿል።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመረጃ ማዕከል እንዲሁም የአጭር መልዕክት አሰራሮችም በውይይቱ ይዳሰሳሉ ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
በቀጣይ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከልም የመራጮች ምዝገባና የአስፈጻሚዎች መረጃን ጨምሮ በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!