የሀገር ውስጥ ዜና

በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

By Tibebu Kebede

March 03, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ በማገዶ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ።

በትናትናው ዕለት በከተማዋ በደረሰ የእሳት አደጋ 29 መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ቤት መውደማቸው ተጠቁማል።

የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በዳሶ ታደሰ የእሳት አደጋው በኤሌክትሪክ ሀይል ምክንያት ሳይከሰት እንደማይቀር ገልፀዋል።

በአደጋው የ19 አባወራዎች ንብረት ሙሉ በሙሉ መውደሙን ሃላፈው ተናግረዋል።

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- ወረዳhttps://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!