የሀገር ውስጥ ዜና

በግዥ ዕቅድና ንብረት አስተዳደር በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

March 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ግዥን በዕቅድ በመምራት የንብረት አስተዳደርን ውጤታማነት እናሳድግ” በሚል መሪ ቃል በግዥ ዕቅድና ንብረት አስተዳደር በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እያደረገ ያለው ውይይት በገንዘብ ሚኒስቴር አዳራሽ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የውይይት መድረኩ በመንግሥት ግዥ ዕቅድና ንብረት አስተዳደር በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ያተኮረ ነው።

በመድረኩም ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ መከላከያ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ፣ ግብርና ሚኒስቴር፣ ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲና ሌሎች የፌዴራል ተቋማት ተሳታፊ መሆናቸውን አብመድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!