የሀገር ውስጥ ዜና

የማህጸን በር ካንሰርን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ  እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

By Meseret Demissu

March 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህጸን በር ካንሰርን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አሳሰበ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የእናቶች የማህጸን በር የቅድመ ካንሰር ልየታ እና የህክምና አገልግሎት የንቅናቄ ፕሮግራም ተጀምሯል፡፡

ንቅናቄው እድሜያቸው ከ30 እስከ 49 አመት ያሉ እናቶችን በመለየትና ህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን ለውጤታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በአዲስ አበባ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት ከ130 በላይ ጤና ተቋማት መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡

በዚህ ዝግጅት ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!