አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘውና የሆራ አርሰዲ የኢሬቻ በዓል የሚከበርበት አካባቢ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የባህል ማዕከል እየተገነባ መሆኑን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ገልጿል፡፡
የግንባታ ወጪውን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የሚሸፍን ሲሆን፤ የማዕከሉ ዲዛይን የኦሮሞን ባህልን በሚገልጽ ሁኔታ መቀረጹም ተገልጿል፡፡
የባህሉ ማዕከሉ አዳራሽ፣ የምግብ ቤቶች፣ የንግድ ሱቆች፣ የመዝናኛ ቦታዎችና ሌሎች አስፈላጊ መስፈርቶችን ያሟላ ተደርጎ ይሰራል መባሉን ኢብኮ ዘገቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!