የሀገር ውስጥ ዜና

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ልዑካን ቡድን በህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተመለከተ ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ተወያዩ

By Meseret Demissu

March 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ልዑካን ቡድን በህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በተመለከተ ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚስቴር ጋር ተወያይተዋል ፡፡

ውይይቱ የተካሄደው በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት  መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ትሺሴኬዲኪ የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ናቸው ፡፡ የልኡኩ አባላት ከዶ / ር ኢ/ር ስለሺ በቀለና ከከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ወቅታዊ

ሁኔታና የሶስትዮሽ ድርድርን አስመልክቶ ተወያይተዋል ፡፡

ሚንስትሩም ኢትዮጵያ ለጋራ ተጠቃሚነትና መፍትሄ  ትሰራለች በድርድሩ ረገድም ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

አመራርን በጉጉት ትጠብቃለች ሲሉ ተናግረዋል ፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ በሶስትዮሽ ድርድሩ ለአፍሪካ ችግሮች ለአፍሪካዊ መፍትሄዎች ለማምጣት ቁርጠኛ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!