አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኮቪድ-19 ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማሰራጨት እየተደረገ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ ውይይት ተደርጓል፡፡
ከተለያዩ ተቋማት የተዋቀረው ሀገራዊ የኮቪድ-19 ክትባት የበላይ አስተባባሪ ኮሚቴ ክትባቱን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባትና ለማሰራጨት እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ ዝግጅት ላይ ተወያይቷል፡፡
የኮቪድ -19 ክትባት አቅርቦትና ስርጭት አስመልክቶ በታቀደው መሰረት የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትና ያለው ዝግጁነት በዝርዝር የቀርበ እና የተገመገመ ነው፡፡
ክትባቱ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን በተቆጣጣሪ አካል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች፣ እንዲከተቡ የተለዩ አካለትን አስመልክቶና አስፈላጊውን ግንዛቤ ለማህበረሰቡ ለመፍጠር የተሰሩ ስራዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ በቀጣይ ትኩረት አግኝቶ ሊከናወኑ የሚገቡ ጉዳዮች ተለይቶ በጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አቅጣጫ ተሰጥተዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የጤና ሚኒስትር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አጄንሲና የተለያዩ የልማት አጋር ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች መሳተፋቸውን ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!