የሀገር ውስጥ ዜና

በምርጫው ሂደት የሚሳተፉ ሴቶች ጾታን መሰረት ላደረገ የጥላቻ ንግግር እና ጥቃት እንዳይጋለጡ መከላከል ይገባል – ኢሰመኮ

By Abrham Fekede

March 08, 2021

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዘንድሮው ሀገራዊ የምርጫ ሂደት የሚሳተፉ ሴቶች ጾታን መሰረት ላደረገ የጥላቻ ንግግር እና ሌሎች ጾታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲከላከሉ ጥሪ አቀረበ፡፡

ኮሚሽኑ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት /ተመድ/ የሥርዓተ-ጾታ እኩልነት እና የሴቶች መብቃት ድርጅት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች ላይ በፌደራል ደረጃ በአዲስ አበባ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች የዳሰሳ ጥናት ማድረጉን ጠቅሷል፡፡

ጥናቱም ሴቶች የተለያዩ ሥነ-ልቦናዊ፣ አካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ብሎም ወሲባዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱባቸው አሳይቷል ነው ያለው፡፡

እንዲሁም ሴት የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች ለእነዚህ ጥቃቶች ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

ለዳሰሳው ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው ሴቶች በፖለቲካ ተሳትፏቸው ምክንያት የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶቻቸውን መነጠቃቸውን፣ እስር፣ አካላዊና ጾታዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው፣ ከእምነት ቦታዎቻቸው መታገድ ጀምሮ እስከ በቤተሰብ መገለል ድረስ ለተለያዩ ችግሮች እንደተዳረጉ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በማኅበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ድረገጾች የፖለቲካ አቋማቸውን የሚገልጹ ሴቶችም ሆኑ በቀጥታ በምርጫው የሚሳተፉ ሴቶች በጾታቸው ላይ ላተኮሩ፣ በአካላዊ ቁመናቸው፣ በአለባበሳቸው ብሎም በማኅበራዊ ሕይወታቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ ለሚያነጣጥሩ ዘለፋዎችና ሥነልቦናዊ ጉዳት ለሚያደርሱ የጥላቻ ንግግሮች እንደሚጋለጡ መግለጻቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/…/www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

በምርጫ ሂደቶች የሚሳተፉ ሴቶችን ከጥላቻ ንግግር እና ጾታዊ ጥቃት