የሀገር ውስጥ ዜና

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጣልቃ ገብነት እና የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት በመቃወም  በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ አካሄዱ

By Tibebu Kebede

March 10, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአንዳንድ አካላትን ጣልቃ ገብነት እና መጠነ ሰፊ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመቃወም በዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ አካሄዱ።

በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተው የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ  የኢትዮጵያን ገፅታ ከማበላሸቱ ባሻገር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ዝቅ ያደረገ በመሆኑ እውነትን ለማውጣት እንደሚታገሉ አስታውቀዋል።

አንድነት ለኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል በዋሽንግተን ዲሲ የተካሄደ ሲሆን በነገው ዕለትም በኒውዮርክ ሌላ ሰልፍ ይደረጋል።

የዋሽንግተን ዲሲ ሰልፍ ተሳታፊዎች የተለያዩ መልዕክቶችን በመያዝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

የሰልፉ አስተባባሪዎች ጣሰው መልካህይወትና ቢንያም ጌታቸው  የጁንታው ርዝራዦች እና እነሱን የሚደግፉ መገናኛ ብዙሃን በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃውን ተከትሎ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለማሳሳት ጥረት እያደረጉ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የትግራይ ክልል መልሶ ለመገንባት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ የሚከናወነውን ተግባር  እውቅና ሳይሰጡ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!