አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ከፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደሚጀምር የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ክትባቱ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት እንደሚሰጥም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
ጤና ሚኒስቴር ክትባቱን ለመጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡
እስካሁን ስልጠና መስጠት፣ ክትባቱን ማሰራጨትና ክትባቱን መውሰድ የሚገባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የመለየቱ ተግባርና ሌሎችም ዝግጅቶች በስፋት ማከናወኑንም አስታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ 19 ክትባት በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት መረከቧ ይታወሳል፡፡
በመጀመሪያ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከፍ ያሉ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!