አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ተጨማሪ 300 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ጂዳ ከተማ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
መንግስት ከሳዑዲ አረቢያ እና ከሌሎች ሀገራት በችግር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን እየመለሰ ይገኛል።
በዚህም በቅርብ ጊዜያት ከሳዑዲ እና ሊባኖስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የሚታወስ ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!