አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በጋራ ህንፃ የማህበር ቤት አሰራር መመሪያና ምዝባውንም ለማከናወን በተዘጋጀው የኮምፒዩተር ፕሮግራም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በከተዋማ በ2005 ዓ.ም የ20/80 እና የ40/60 የቤት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች በጋራ ህንፃ መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ተጠቃሚ ለማድረግ የወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2013 ዓ.ም መሰረት በማድረግ ነው የግንዛቤ መስጨበጫ መድረኩ እየተካሄደ ያሚገኘው፡፡
በከተማዋ የሚታየው የቤት ችግርን ለመፍታት በራስ አገዝ በማህበር በማደራጀት ዜጎች ቤት እንዲሰሩ ያለመው የህብረት ስራ ማህበር መመሪያው ሲዘጋጅ የመጀመሪያ ዙር ተጠቃሚ የሚሆኑት በ2005 ዓ.ም በጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ናቸው ተብሏል፡፡
መመሪያው በቤት ልማት ፕሮግራሙ ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች አቅምና ፍላጎት ያላቸውን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ገንዘባቸውን እውቀታቸውን ጊዜያቸውን በማቀናጀት የቤት ችግሮቻቸውን በጋራ ጥረት እንዲፈቱ የሚችሉበትን አማራጭ መፍጠር ያስችላል ተብሏል፡፡
በግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኩ የተጠቃሚ ተወካዮችንና ባለድርሻ አካላትን ያገናኘ ሲሆን፣ ይህ የማህበር ቤት አሰራር እንደ አንድ አማራጭ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትንና አቅርቦትን ለማጣጣም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡
መመሪያውን ተከትሎ የጋራ ቤቶችን ለመገንባት መሰረታዊ ችግሮች ናቸው ተብለው በተለዩ የመሬት አቅርቦትና ፋይናንስ ጉዳይ ላይም ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!