አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሳህራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሳሌም ኦልድ ሳሌክ ጋር ተወያዩ፡፡
አቶ ደመቀ ውይይቱን ያካሄዱት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እና ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ልዩ ልዑክ ጋር ነው፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሳሌም ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት የተላከ የመልካም ምኞት መልዕክት ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ አስተላልፈዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በጋራ ጉዳዮችና የሳሃራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ስለ ኢትዮጵያ ሚና ተወያይተዋል፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት በተመድ ቻርተርና በአፍሪካ ህብረት አዋጆች እና መርሆዎችን መሰረት ያደረገ ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊ የሆነ በሁለት ወገን ተቀባይነት ያለው መፍትሔ እንደሚደግፍ ገልጸውላቸዋል፡፡
በተጨማሪም የአፍሪካ ህብረት በሰላም ሂደቱ ዙሪያ በሚጫወተውን ሚና የሚደገፍ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያም የበኩሏን ለማበርከት ዝግጁ መሆኗን ነው ያስታወቁት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!