የሀገር ውስጥ ዜና

ሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን ተስፋ ያላቸው አህጉራዊ ስራ ፈጣሪዎች ተብለው ሽልማት ተበረከተላቸው

By Tibebu Kebede

March 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያን ተስፋ ያላቸው አህጉራዊ ስራ ፈጣሪዎች ተብለው ሽልማት ተበረከተላቸው።

ጄትኤጅ ኔሽን ቢውልደር የተሰኘ ድርጅት ሽልማቱን በአዲስ አበባ ባካሄደው ስነ ስርዓት ላይ አበርክቷል።

የቀበና ሌዘር መስራች ሰመሀል ግዑሽ ሽልማቱ ከተበረከተላቸው አፍሪካውያን መካከል አንዷ ሆናለች፡፡

የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ጄትኤጅ ኔሽን ቢውልደር ጋር በመተባበር ወጣቶችን ለማበረታታትና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!