አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር (አልማ) ከ7ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ ፡፡
የአልማ የዲያስፖራ በጎ ፈቃደኞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ጉታ ÷ ድጋፉን በካናዳ የሚኖሩ የማህበሩ አባላት ማሰባሰባቸውን ገልፀዋል ፡፡
ለኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ ማስጀመሪያ አጋዥ የሆኑ የኩላሊት እጥበት ማሽን፣ዊልቸር ስትሬቸር እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል ፡፡
ሆስፒታሉ በ172 ሚሊየን ብር ተገንብቶ አገልግሎቱን ለመጀመር ከክልሉ መንግስት እና ከአጋር አካላት እስካሁን ከ3 ነጥብ 5ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ መገኘቱን የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ አቶ ከበደ ይመር ተናግረዋል፡፡
ከ1 ነጥብ 5ሚሊየን በላይ ለሚሆን የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እንደሚሰጥ የሚጠበቀው ሆስፒታሉ በመጋቢት ወር መጨረሻ በተመላላሽ ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል ፡፡
በሰብለ ሲሳይ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!