የሀገር ውስጥ ዜና

242 ሺህ 605 የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች በሰበታ ከተማ ተያዘ

By Tibebu Kebede

March 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰበታ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከ242 ሺህ 605 የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች መያዙን አስታወቀ፡፡

ገንዘቡ በግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አበራ ዳባ አስታውቀዋል፡፡

ከተያው ገንዘብ ውስጥ 36 ሺህ 678 የአሜሪካ ዶላር፣ 59 ሺህ 150 የሳዑዲ ሪያል፣ 84 ሺህ 785 የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ድርሃም፣ 5 ሺህ 570 የካናዳ ዶላርን ጨምሮ የበርካታ ሃገራት ገንዘቦች መያዙንም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!