የሀገር ውስጥ ዜና

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ስራ ድጋፍ እንደሚሰጥ ገለጸ

By Meseret Demissu

March 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ )የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ባደረገው ስብሰባ ማጠቃለያ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ስራ ድጋፉን ሰጠ፡፡

ምክር ቤቱ በተለይም ኮሚሽኑ ለሚያቀርባቸው ዝርዝር መረጃዎች እንዲሁም ተግባራዊ እንዲደረጉ ለሚሰጣቸው ምክረ ሀሳቦች ድጋፉን ሰጥቷል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በትግራይ በተጨባጭ ያለው ሁኔታ ላይ ክትትሉን እንዲቀጥል ማበረታታቱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!