የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሃገር አቀፍ ደረጃ መሰጠት ጀመረ

By Tibebu Kebede

March 13, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሃገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው እለት መሰጠት ጀምሯል፡፡

ክትባቱ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው የተጀመረው፡፡

በክትባት ማስጀመሪያ ስነ ስርአቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የተመድ የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች እና የተለያዩ የጤናው ዘርፍ አጋሮች ተገኝተዋል፡፡

የመጀመሪያውን ዙር ክትባት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተከትበዋል፡፡

በቆንጅት ዘውዴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!