የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ለመቀየር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ

By Meseret Awoke

March 13, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ለመቀየር የቀረበውን አዋጅ አፅድቋል።

በቀጣይ 6 ወራት በጥናት ላይ ተመስርቶ የአማራ ህዝብን ታሪክና ስነ ልቦና የሚያንፀባርቅ ሰንደቅ ዓላማ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውልም ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።

ነባሩ ሰንደቅ ዓላማ አንድን ፓርቲ የሚወክል እንጂ የአማራ ህዝብን ስነ ልቦና የማያንፀባርቅ በመሆኑ በህዝቡ ተቀባይነት ማጣቱም በምክር ቤቱ ተገልጿል።

እንደ ኢብኮ ዘገባ ምክር ቤቱ 3ኛ ቀኑን በያዘው 17ኛ መደበኛ ጉባኤው የቴምብር ቀረጥ ማሻሻያ አዋጅንና የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን ገምግሞ አፅድቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!