የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምዕራብ አርሲ ዞን በመስኖ የለማን የስንዴ ሰብልን ጎበኙ

By Meseret Awoke

March 13, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2013 ዓም (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በምዕራብ አርሲ ዞን ኤበን አርሲ ወረዳ ሾባ ቡልቱም ቀበሌ በመስኖ የለማን የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፤የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለ ማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በኤበን አርሲ ወረዳ 1 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በስንዴ ምርጥ መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ካሳሁን ገለቶ ገልጸዋል።

ሃላፊው በወረዳው ከስንዴ በተጨማሪ 4 ሺህ 300 ሄክታር መሬት በሽንኩርት፤ቲማቲም ፤ ድንች እና በሌሎች ምርቶች ተሸፍኗል።

በአካባቢው ለመጀመሪያ ጊዜ መስኖን በመጠቀም የግብርና ስራው ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች መንግስት የትራክተር፤ መዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ማቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!