አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርጫ ክርክርን ሊያዘጋጁ የሚችሉ 11 ድርጅቶች መመረጣቸውን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ቦርዱ ባወጣው የፍላጎት ማቅረቢያ ቀነ ገደብ 23 ድርጅቶች ለማወያየት ጥያቄ አቅርበው ነው 11ዱ መመረጣቸው ተነግሯል።
ድርጅቶቹም÷
1 ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት
2 አሃዱ ቴሌቪዥን
3 ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ
4 ሴታዊት ሙቭመንት
5 የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች
6 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ጉባኤ
7 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት
8 ኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲሴብሊቲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን
9 የኢትዮጵያ መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች ማህበር
10 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን
11 ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ ናቸው።
ፓርቲዎች ከተመረጡት ውጭ ባሉ መድረኮች የመከራከር መብት እንዳላቸው ቦርዱ አስታውቋል።
የብዙሀን መገናኛ ተቋማት የሚያዘጋጁት ክርክር የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከሚደለደለው የቅስቀሳ ሰዓት ጋር የሚገናኝ አይደለም ተብሏል ።
በአላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!