የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም የውሃ ቀን ለ27ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው

By Tibebu Kebede

March 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2021 የዓለም የውሃ ቀን “ለውሃ ዋጋ መስጠት” በሚል መሪ ቃል ለ27ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው።

ቀኑ የውሃ ቀውስ ግንዛቤን ለማዳበር እና የውሃ እና የአካባቢ ጽዳትን ለሁሉም ማረጋገጥ የሚለውን እቅድ ለማሳካት እና ለመደገፍ በማለም ነው የሚከበረው።

ቀኑ ሲከበር የውሃ ምንጮችን ዋጋ መስጠት፣ ትኩረት ለውሃ መሰረተ ልማት፣ ለውሃ አገልግሎትና ስራዎች ዋጋ መስጠት በሚሉት ጉዳዮች ላይ ምክክር ሲያካሂድ ውሃን የማህበራዊ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ አካል አድርጎ መንቀሳቀስ bሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።

በአሁኑ ወቅት ዓለም ላይ በግጭት፣ በመፈናቀልና በልዩ ልዩ ችግሮች ምክንያት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ ሰዎች ንጹሕ ውሃ እንደማያገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።

የዓለም የውሃ ቀን ከፈረንጆቹ 1993 ጀምሮ በየአመቱ መጋቢት 22 ቀን ይከበራል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!