የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ በረራ ከ1 ሚሊየን በላይ ብልቃጥ የኮቪድ 19 ክትባት አጓጓዘ

By Tibebu Kebede

March 31, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ በረራ 1 ሚሊየን 55 ሺህ ብልቃት የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማጓጓዙን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ክትባቱን ከቤጅንግ ወደ ዚምባቡዌ ዋና ከተማ ሀራሬ በአዲስ አበባ በኩል አድርጓ እንዳጓጓዘ  ወርልድ ኤር ወይስ ዘግቧል።

በተመሳሳይ በትናትናው ዕለት አየር መንገዱ ከቻይና ለኢትዮጵያ የተለገሰ 300 ሺህ ብልቃጥ ክትባት ወደ አዲስ አበባ መጓጓዙ የሚታወስ ነው።

ቦሌ አለም አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የህክምና አቅርቦቶችን ለማሰራጨት መመረጡ የሚታወስ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!