የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የግንባታ ሂደት እየጎበኙ ነው

By Tibebu Kebede

April 06, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተለያዩ ሳይቶች በግንባታ ላይ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የግንባታ ሂደት እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉብኝቱ በዘጠኝ ሳይቶች የሚገኙ የ40/60 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የግንባታ ሂደት ያሉበትን ደረጃ ነው እየተመለከቱ ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!