የሀገር ውስጥ ዜና

የትራፊክ ቅጣት በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

By Meseret Awoke

April 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የትራፊክ ቅጣትን በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።

መተግበሪያው የአገልግሎት አሰጣጡን ፈጣንና ቀልጣፋ በማድረግ አሽከርካሪዎችን ከእንግልት የሚታደግ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጅሬኛ ሄርጳ ተናግረዋል፡፡

የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ባሉበት ቦታ ሆነው መክፈልም ይችላሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ክፍያውን በኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክና የኢ-ብር አገልግሎት በሚሰጡ የግል ባንኮች በኩል መፈጸም እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!